Monday, February 18, 2019

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ: አርባ ምንጭና ተሰሎንቄአዊ ልቧ

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ: አርባ ምንጭና ተሰሎንቄአዊ ልቧ:    Please read in PDF በኹለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው፣ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወንጌል በመመስከር ካለፉባቸው ከተሞች አንዷ ተሰሎንቄ ናት፤ “ በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ...

Thursday, December 14, 2017

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ባሳተመቻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ ለሮሜ.8፡34(የሚማልድ ወይስ የሚፈርድው) የትርጉም መበላሽት ተጠያቂው ማን ነው?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ባሳተመቻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ ለሮሜ.8፡34(የሚማልድ ወይስ የሚፈርድው) የትርጉም መበላሽት ተጠያቂው ማን ነው?
              የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በግዚያቱ  ባሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንድ ጥቅሶች በከዚ ቀደም ከታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ጋር አንድ አይደሉም፣ ወይም ተቀይረዋል። ለዚህም አንዳንድ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ።

በ1980ዓ.ም ባሳተመችው መጸሓፍ ቅዱስ መጽሐፉ መግቢያ ላይ "ከቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ የሆኑ ባዕዳን ቃላት" ከመጽሐፍ ቅዱሱ እንደተወገዱና የተዘለሉ ካሉም በአንባብያን ጥቆማ ዳግም 'እንደሚስተካከሉ' ይገልጻል። ይህም የግለሰቦች ሳይሆን የሲኖዶሱ እጅ እንዳለበት ጭምር ስለሚናገር በቀላል የሚታይ ጉዳይ አይደለም።

በመጽሐፉ የውስጥ ገጾች ውስጥ እነዚህ ባእዳን ተብለው ከተቀየሩት አብዛኞቹ ከሌላኛው ጽሁፍ ደመቅ ብለው ይታያሉ። ይህም የቅርጸ-ቁምፊ (ፎንት) ልዩነት ያመጣው ውጤት እንደሆነ መጠርጠር ይቻላል።

ከተለወጡት ጥቅሶች አብዛኞቹ ከምልጃ እምነት ጋር የማይጣጣሙ በመሆናቸው እንደሆነ በቀላሉ መገንዘን ይቻላል።አንዳንዶቹም ከማርያም ጋር የተያያዙ ናቸው።

የዚህ ለውጥ መሰረት ምን ነበር? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ እትም ከስህተት የጸዳ ነው የሚል አመለካከት የለኝም። የተርጓሚዎቹ እምነት ተጽዕኖ አሻሚ በሆኑ ቦታዎች ላይ በመጠኑም ቢሆን እንዳለበት የሚካድ አይደለም። የዚህኛው ግን አይን ያፈጠጠ ክህደት እንደሆነ መገንዘብ ቀላል ነው።

የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጻፈበት ቋንቋ ግሪክኛ ነው። ምናልባት አንዳንዶች በግሪኩ የተጻፈውን ቃል በትክክል ለማሰቀመጥ ነው ይሉ ይሆናል። ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም። ከላይ በጠቀስኳቸው ጥቅሶች ላይ የተሰራውን ለውጥ በሚመለከት የግርጌ ማስታወሻዎች ገብተዋል። እነዚህ የግርጌ ማስታወሻዎች "በግሪኩ እንዲህ ይላል" በማለት አሁን በመጽሐፍ ቅዱሳችን (1954ቱን ማለቴ ነው) ላይ ያለው ትክክል እንደነበር ይገልጻሉ! "በግሪኩ" የሚለውን አገላለጽ የማይረዱ ብዙዎች ስለ እውነታው ምን እንደሚያስቡ ገምቱ።

ለዛሬ በሮሜ 8፡34 ላይ ለስራችው ክህደት ግልጽ መረጃ በማቅረብ ቤተክርስቲያንዋን ለንስሀ እነጠራለን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ  የተጻፈበት ቋንቋ ግሪክኛ አንደመሆኑ እና በመላው ዓለም  ያሉ ዋና ቋንቋዎች ለመጠቀም ተግደናል ፡  


Geeze


መኑ ዘይኳንን ክርስቶ ኢየሱስ ሞተ ወተንሥአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚያብሔር ወይትዋቀሥ በእንቲአነ፡፡
ወይትዋቀሥ በእንቲአነ፡፡
ስለኛ ይከራከራል

 GREEK  

τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς Ἰησοῦς ὁ ἀποθανών, μᾶλλον δὲ ἐγερθείς, ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
ἐντυγχάνει
የሚማልደው

HEBREW

ומי הוא יאשימם הן המשיח אשר מת וביותר אשר נעור מעם המתים הוא לימין האלהים והוא יפגיע בעדנו׃
የሞቱ መሲሁንና ከሙታን የሚነሡት እነማን ናቸው? እርሱ የእግዚአብሄር ቀኝ ነው :: 
እርሱ ለእኛ ይጸልይልን

 LATIN

 quis est qui condemnet Christus Iesus qui mortuus est immo qui resurrexit qui et est ad dexteram Dei qui etiam interpellat pro nobis
ስለ እኛ የሚማልደው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ማን ሞተ, እና ከዚህም በላይ ደግሞ የተነሣው ክርስቶስ ማን ነው
Dei qui etiam interpellat pro nobis
ለእኛ ይማልድልናል

ARABIC
 
 من هو الذي يدين. المسيح هو الذي مات بل بالحري قام ايضا الذي هو ايضا عن يمين الله الذي ايضا يشفع فينا
 የሞተው: ይልቁንም ከሙታን የተነሣው: በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው: ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው
 ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
 ايضا يشفع 
   እሱም ይማልዳል
 
English
 
Who is he that condemns? Christ Jesus, who died—more than that, who
 was raised to life
—is at the right hand of God and is also interceding for us.

የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

 interceding for us.
የሚማልደው

FRENCH
Christ est mort; bien plus, il est ressuscité, il est à la droite de Dieu, et il intercède pour nous!
ክርስቶስ ሞቷል; ከዚህም በተጨማሪ እርሱ ተነስቷል; እርሱ በእግዚአብሔር ቀኝ ይገኛል, ስለኛም ይማልዳል!
et il intercède pour nous!
ለእኛም ይማልዳል!
 
Russian

Христос Иисус умер, но и воскрес: Он и одесную Бога, Он и ходатайствует за нас.
ክርስቶስ ኢየሱስ ነው የሞተው ግን ተነሥቷል: እርሱ በእግዚአብሔር ቀኝ ነው, ስለ እኛም ይማልዳል.

Он и ходатайствует за нас.   
እርሱ ይማልዳል.
 
GERMEN

Christus ist hier, der gestorben ist, ja vielmehr, der auch auferweckt ist, welcher ist zur Rechten Gottes und vertritt uns.
ሊፈረድበት  የሚፈልገው  ማን ነው? የሞተው: ይልቁንም ከሙታን የተነሣው: በእግዚአብሔር  
ቀኝ ያለው: ደግሞ  
ስለ  እኛ  የሚማልደው ክርስቶስ  ኢየሱስ  ነው፡፡
 
welcher ist zur Rechten Gottes und vertr
በእግዚአብሔር  ቀኝ  ያለው: ደግሞ  ስለ  እኛ  የሚማልደው ክርስቶስ  ኢየሱስ  ነው፡፡
 
CHINESE

有基督耶穌已經死了,而且從死裡復活,現今在神的右邊,也替我們祈求
የሞተው: ይልቁንም ከሙታን የተነሣው: በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው: ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው
 ክርስቶስ ኢየሱስ ነው.
也替我們祈求。
ለእኛም ይጸልይልን.
Amharic bible
Amharic  1879

ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን፡፡ ከሙታንም እንኳ የተነሣ በእግዚያብሔር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም ያስምረናል፡፡

Amharic  1927

ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን፡፡ ከሙታንም እንኳ የተነሣ በእግዚያብሔር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም ያስምረናል፡፡

Amharic  1938

ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ በአብ ቀኝ ተቀምጦአል ስለ እኛ ይፈርዳል፡፡

Amharic  1947

በእግዚአብሔር  ቀኝ  ያለው: ደግሞ  ስለ  እኛ  የሚማልደው ክርስቶስ  ኢየሱስ  ነው፡፡

Amharic  1954

በእግዚአብሔር  ቀኝ  ያለው: ደግሞ  ስለ  እኛ  የሚማልደው ክርስቶስ  ኢየሱስ  ነው፡፡

Geeze and Amharic  1975

ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ በእግዚያብሔር ቀኝ ተቀምጦአል ስለ እኛም ይፈርዳል፡፡

Amharic  1980

በእግዚአብሔር  ቀኝ  ያለው: ደግሞ  ስለ  እኛ  የሚማልደው ክርስቶስ  ኢየሱስ  ነው፡፡

Amharic  2000

የሞተው ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሣው በእግዚያብሔር ቀኝ የተቀመጠው ደግሞ ስለኛ ሚፈርድወ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

ይህን ያክል ካይን የሚፈርድ የሚለው ቃል የሚገኝው በአማረኛው ዕትም ያውም በ1938 ፤በ1975፤ እና በ2000ዓ.ም ባሳተመችው መጸሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ መሆኑን እነመለከታልን ግዕዙን ጨምሮ ሁሉም የዓለማችን ቋንቋዎች የሚማልደው ሲሉ በአማረኛው መጸሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ የሚፈርደው ማለቱ ያሳዝናል  በእግዚያብሔር ቃል ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስ ፍረድ አለበት ቤተክርስቲያኒቱ ከዚ ዓይነ ያፈጠጠ ክህደት እድተመለስ እነለምናታልን
ጌታ ሆይ ቶሎ ና





Monday, May 23, 2016

"ኢየሱስ ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን መካከለኛ"


ትምህርተ ተዋሕዶ ምን ይላል?[3]
“ክርስቶስ አሁን መካከለኛ አይደለም” የሚለው ኑፋቄ ምንጩ የአውጣኪ ትምህርት መሆኑ ይታወቃል። አውጣኪ በአንዱ በክርስቶስ የቃልና ሥጋ መደባለቅ (ቱስሕት)፣ የሰውነት ወደ አምላክነት መለወጥ (ውላጤ) ወይም መለዋወጥ (ሚጠት) ተከናውኗል ብሎ የተነሣ መናፍቅ ሲሆን፣ እርሱም ትምህርቱም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተወግዘው ከተለዩ ብዙ ምእት ዓመታት ተቈጥረዋል። በእርሱ የኑፋቄ ትምህርት አንጻር ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ትምህርተ ተዋሕዶን አምልተውና አስፍተው አስተምረዋል።
የተዋሕዶ ትምህርት “አንቀጸ ተዋሕዶ” እንደሚባል ሊቃውንቱ ያስረዳሉ። ተዋሕዶ ሊገኝ የቻለውም አንቀጸ ተከፍሎን መነሻ በማድረግ ነው ሲሉ ያክላሉ። እንደ ሊቃውንቱ ማብራሪያ የአንቀጸ ተከፍሎ ትምህርት የሚያመለክተው ከተዋሕዶ በፊት የነበረውን የሥግው ቃልን ባሕርያውያን ምንጮችን ነው። ይኸውም ከሁለት ባሕርያተ ልደታት፣ ማለትም ቃል እም ቅድመ ዓለም ከአብ መገኘቱን፣ ትስብእትም ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም አብራክ መገኘቱን (መከፈሉን) ነው። በጥቅሉ የሁለቱም ምንጭና ተረክቦ (መገኘት) የሚታሰበብትን ጊዜ ያሳያል። አንቀጸ ተከፍሎን ፊልክስ ሰማዕት እንደሚከተለው አብራርቷል፤ “ወካዕበ ይቤ ንጠይቅ ክፍላተ ፪ቱ ህላዌያት ወስመ ፪ቱሂ ክፉል በኵሉ ጊዜ በምግባር ወበነገር ዘውእቶሙ መለኮት ወትስብእት። ወሶበ ንቤ ከመዝ ኢይምሰልክሙ ዘንከፍሎ እም ድኅረ ፩ዱ ከዊን ወዳእሙ ናጤይቅ ህላዌ መለኮት ወህላዌ ትስብእት ወዓዲ ነአምር እስመ ቃል አኮ ዘተመይጠ እም ህላዌ መለኮቱ ለከዊነ ትስብእት ሶበ ኀደረ ላዕሌነ። - ዳግመኛ [ቅድመ ተዋሕዶ የነበረ] የሁለቱን ባሕርያት (የመለኮትንና የትስብእትን) ልዩነት፣ የሁለቱም ስም በጊዜው ሁሉ በሥራ በአነጋገር ልዩ እንደ ነበረ እንወቅ፤ እነዚህም መለኮትና ትስብእት ናቸው። እንደዚህም ባልን ጊዜ ከተዋሕዶ በኋላ የምንለየው አይምሰላችሁ፤ የመለኮትን ባሕርይ የትስብእትን ባሕርይ እናስረዳለን እንጂ፤ ዳግመኛም ቃል ባሕርያችንን በተዋሐደ ጊዜ ከመለኮቱ ባሕርይ ሥጋ ወደ መሆን እንዳልተለወጠ እናውቃለን።” (ሃይማኖተ አበው 1986፣ ገጽ 131)።
“በዚህ መሠረት የአንቀጸ ተዋሕዶ ትምህርት በአንቀጸ ተከፍሎ መሠረት ከጥንት ተለያይተው ከኖሩ ከሁለቱ … የአንዱን የዐማኑኤልን ህላዌ ቅውም አድርጎ የሚያሳይ የምስጢረ ተሠግዎ ወይም የምስጢረ ተዋሕዶ ትምህርት ነው።”[4] ስለዚህ በተከፍሎ የነበሩት ከተወሐዱ በኋላ አንዱን ከሌላው መለየትና እየብቻቸው ማድረግ አይቻልም። ቄርሎስ ይህን ሲያስረዳ እንዲህ ብሏል፤ “ኢትፍልጥ ሊተ እም ድኅረ ትድምርት እስመ ዘፈለጠ እንተ ባሕቲቶ ብእሴ ወእንተ ባሕቲቶ አምላከ ቃለ ክልኤተ ይሬስዮ ለዐማኑኤል። - ከተዋሕዶ በኋላ አትለይብኝ፤ ከተዋሕዶ በኋላ ብቻውን ሰው፥ ብቻውን አምላክ ቃል የሚል ሰው ቢኖር ዐማኑኤልን ሁለት ያደርገዋል።”[5]
የአንጾኪያው ባስልዮስም፣ “አይትከፈል ኀበ ክልኤቱ ህላዌያት እም ድኅረ ተዋሕዶ እስመ ለምንታዌ አእተታ ተዋሕዶ፤ ወተዋሕዶኒ ያግሕሥ ኵነኔሁ ለምንታዌ እስመ ውእቱ ተዋሕዶ አካላዊ ዘኢይትከፈል። - ከተዋሕዶ በኋላ ወደ ሁለት ህላዌያት አይከፈልም፤ ተዋሕዶ መንታነትን አስወግዷልና፤ የመንታነትንም ፍርድ አርቋል። እርሱ የማይከፈል አካላዊ ተዋሕዶ ሆኖአል” ብሏል (ሃይማኖተ አበው 1986፣ ገጽ 422)።
ከእነዚህ ምስክርነቶች ስለ ወልድ ከትስብእትና ከተዋሕዶ በፊት ስለ ነበረው አቋም በአንቀጸ ተከፍሎ ሊነገር እንደሚገባና ከተዋሕዶ ወዲህ ስላለው አቋሙ ደግሞ በአንቀጸ ተዋሕዶ ሊነገር እንደሚገባ እንረዳለን። ምስጢረ ተዋሕዶ የተከናወነው በተለመደውና በሚታወቀው የውሕደት ሕግ ሳይሆን በሕገ ተዐቅቦ ነው። “ተዐቅቦ ማለት በቀላል አገላለጽ መጠበቂያ ማለት ነው። ለምሳሌ መጠበቂያ ያለው ነገር ከተፈለገ፣ ለጊዜው የጠመንጃ ሁኔታ ሊታወስ ይቻላል። ጠመንጃው ጥይት ጐርሶአል እንበል። ነገር ግን በአስፈላጊው ሁኔታና ጊዜ ምላጩ ተስቦ እስኪተኰስበት ድረስ መጠበቂያ ይደረግበታል። መጠበቂያም ስላለው፣ ምላጩን ወይም ቃታውን ሲስቡ፣ ጥይቱ አይተኰስም፤ አይባርቅም። ለዚያውም (ለተኳሹም) ለሌላውም ሰው ጕዳት አያስከትልበትም። መጠበቂያው እንዳይተኰስ ጠብቆታልና። እንግዲህ የመጠበቂያው መኖር በአስፈላጊነቱ መጠን ጠቀመ ማለት ነው።”[6] በምስጢረ ተዋሕዶ ላይ ሕገ ተዐቅቦ ያስፈለገውም ቃልና ሥጋ እንዲጠባበቁ ለማድረግ ነው። “ተዐቅቦ ተራርቀው ይኖሩ የነበሩትን ባዕል፣ ምሉእና ፍጹም የሆነ አካለ ቃልን እና ድኻ፣ ውሱንና ትሑት የሆነ አዳማዊ ትስብእትን አገናዝቦ የሚገኝ” የምስጢረ ተዋሕዶ መጠበቂያ ነው።
ምስጢረ ተዋሕዶ የተመሠረተው “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ ዐደረ” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ነው (ዮሐ. 1፥14)። እንደ ሊቃውንቱ ማብራሪያ በጥቅሱ ውስጥ የምናገኛቸው “ኮነ” እና “ኀደረ” (ሆነ እና ዐደረ) የሚሉት ቃላት ተዋሕዶንና ተዐቅቦን በኅብረት ይዘዋቸዋል። አንዱ ለብቻው ተነጥሎ ማለትም “ኮነ” ለብቻው “ኀደረ”ም ለብቻው የተዋሕዶን ምስጢር ለመጠበቅ አያስችሉም። ስለዚህ ኮነ እና ኀደረ በአንድነት ምስጢረ ተዋሕዶን የሚጠብቁ ቍልፍ ቃላት ናቸው ማለት ነው። ቃላቱ ለተዐቅቦ ሕግ የተወሰኑት ሁለቱን ነጣጥለው በመጠቀም የተዋሕዶን ምስጢር ያፋለሱትን የንስጥሮስንና የአውጣኪን የተሳሳተ ትምህርት ለማረም መሆኑን ከሊቃውንቱ ማብራሪያ እንገነዘባለን።
ንስጥሮስ ምስጢረ ተዋሕዶን ለመግለጽ ኮነን ትቶ ኀደረን ነው የወሰደው። ስለዚህ “ ‘በአንዱ ክርስቶስ ሁለት ህላዌያት አሉ’ እስከ ማለት ደረሰና ውስጣዊ መለያየትን (ቡዓዴን) እና መከፋፈልን (ፍልጠትን) በምስጢረ ተዋሕዶ ላይ አመጣ። ለዚህም የኮነን እውነተኛ ትርጕም ወይም ፍቺ የያዘና ከኀደረ ጋር የሚያገናኝ መጠበቂያ እንዲኖር አስፈለገ። እነሆም ‘ዘእንበለ ቡዓዴ (ያለመለያየት)፣ ዘእንበለ ፍልጠት (ያለመፈራረቅ/ያለመከፈል)፣ በኢተላፅቆ (ያለመነባበር)’ የሚሉ መጠበቂያዎች፣ የኮነን ምስጢር ይዘው “ኀደረ” ያለውን እንዲጠብቁ ተደረገና የሥግው ቃል ተዋሕዶ ተጠነቀቀ። ለዚህ ለንስጥሮስ ንጥል ሐሳብ ተዐቅቦ ባይደረግበት ለተዋሕዶ ትምህርት አደገኛ ይሆናል። የመጻሕፍት አተረጓጐምም ይጥበረበርበታል።”[7]    
ከንስጥሮስ በተቃራኒ አውጣኪም እንዲሁ ምስጢረ ተዋሕዶን የሚያጠፋ ትምህርት አስተማረ። “በአንዱ ክርስቶስ ቱስሕት (መደበላለቅ)፣ ውላጤ (የሰውነት መለወጥ)፣ ሚጠት (መለዋወጥ) እንዳለበት፣ ሰውነቱ ወደ አምላክነቱ እንደ ተለወጠ ተናገረ። አውጣኪ ኀደረን በመተው የኮነን ፍቺ በተሳሳተ አተረጓጐም ተመለከተና ኮነን ‘ተለወጠ’ በሚል ቃል ተርጕሞ ተሳሳተበት። እንደርሱ ዐሳብ ቢሆን የተዋሕዶን ምስጢር ተዋሕዶንም ደመሰሰበት። ለዚህም መጠበቂያ ልጓም አስፈለገ። እነሆም ‘ዘእንበለ ቱስሕት (ያለመደበላለቅ)፣ ዘእንበለ ውላጤ (ያለመለወጥ)፣ ዘእንበለ ሚጠት ያለመለዋወጥ/ያለመመላለስ)’ የሚሉ ቃላት የኀደረን ምስጢር ይዘው የኮነን ፍቺ ወደ ሌላ እንዳይሄድ፣ ይኸውም በመለወጥ እንዳይተረጐም ይጠብቁ ዘንድ ተደረገ። በዚህም ተዐቅቦ የሥግው ቃል ተዋሕዶ ተጠነቀቀ፤ ታወቀ። ይህ ተዐቅቦ ባይኖር የአውጣኪን ግንጥል ዐሳብ ለተከተለ ሰው የተዋሕዶ እምነቱንና በቅዱሳት መጻሕፍት ያለው የአተረጓጐሙን መንገድ ያቃውስበታል።”[8]
በአጠቃላይ ምስጢረ ተዋሕዶን “የምንጠብቀው በእነዚህ ሕጋውያን የውሳኔ ቃላት መጠበቂያዎች /ሕገ ተዐቅቦ/ ነው። ተዋሕዶ ባለበት ሁሉ ተዐቅቦም ዐብሮት ይገኛል።” ስለዚህ በተዐቅቦ በሆነው ተዋሕዶ አንዱ ክርስቶስ ያለመለያየት፣ ያለመፈራረቅ/ ያለመከፈል፣ ያለመነባበር፣ ያለመደበላለቅ፣ ያለመለወጥ፣ ያለመለዋወጥ ወይም ያለመመላለስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑ ከትምህርተ ንስጥሮስና ከትምህርተ አውጣኪ የተለየ የተዋሕዶ ትምህርት ነው።
ምስጢረ ተዐቅቦን በተመለከተ ቄርሎስ፣ “ኢይደልወነ ንፍልጦ ለ፩ዱ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ውእቱ ብእሲ በዐቅሙ ወለእመኒ ነአምሮሙ ለ፪ቱ ህላዌያት በዘዘዚኣሆሙ ወነዐቅቦሙ ዘእንበለ ቱስሕት በበይናቲሆሙ ንብል እንከ ፩ዱ ውእቱ ክመ ኢየሱስ ክርስቶስ። - በዐቅሙ እንደ ዕሩቅ ብእሲ አድርገን አንዱን ኢየሱስ ክርስቶስ ልንለየው አይገባንም፤ ሁለቱን ባሕርያት በየገንዘባቸው ብናውቃቸውም ያለመቀላቀል በየራሳቸው ብንጠብቃቸው ኢየሱስ ክርስቶስ መቸም መች አንድ ነው እንላለን” (ሃይማኖተ አበው 1986፣ ገጽ 338)።