Tuesday, October 13, 2015

ዘፈን ኃጢአት ነውን?

     በገላትያ 521 “መግደል፣ ስካር፣ ዘፋኝነትበሚለው ጥቅስ ላይ በመመርኰዝ ባሕላዊ ጨዋታና ማንኛውም ለእግዚአብሔር ክብር ከሚቀርብ መዝሙር ውጭ የሆነ ሙዚቃ ኃጢአት ነው የሚል አቋም አጋጥሞን ይሆናል፡፡
ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሃሳብ ከመጓዛችን በፊት ዘፈን በሚለው ቃል ላይ አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ ዘፈን በምንልበት ጊዜ በአአምሮአችን የሚመጣው ምንድን ነው? በቴሌቪዥን ወይም በሬዲዮ የሚቀርቡት ድምጻውያንና የሚያጅባቸው የተወዛዋዦች ቡድን እንደሁም የሚያጅባቸው የሙዚቃ መሳሪያ ነውን? ወይስ ወደ ሲኦል የሚወስድ አስፈሪ ኃጢአት ነው? በፊታችን የሚደቀነው የዚህስ ምክንያቱ ምን ይሆን? እንዳንዴ የሚከብዱ ወይም የሚዘገንኑ ቃላት ወደ ጆሮአችን ሲደርስ እንደሚያጋጥመን ዓይነት ነው ወይስ ኃጢአት ነው ስለተባልን ብቻ ምሥጢሩን ሳንረዳ እንዲሁ በመቀበለ የሚሰማን ነገር ነው?
በመሠረቱ ባሕል የሰው ልጅን ከእንስሳት የሚለይ ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ ማንኛውም ባሕል በክርስቶስ ወንጌል ትምህርት የሚገመገምና የሚፈተን ሲሆን አስፈላጊነቱን ማመን ግን የግድ ይሆናል፡፡ ጌታችን ኢየሱሰ ክርስቶስም እኮ ወደ እኛ የመጣው በአይሁድ ባሕል ውስጥ ተወልዶና አድጎ ነው፡፡ በዚያ ባሕል የተቃወማቸው ነገሮች እንዳሉ ሁሉ የተቀበላቸውም ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በአይሁድ ሠርግ ላይ ባሕላዊ ውዝዋዜ እንደነበረ ይታወቃል፤ ብሉይ ኪዳንም ከሠርግ ጋር ስለሚገናኝ ሙዚቃና ጨዋታ ይናገራል፡፡ ጌታችንም በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ ሲካፈል የሠርግ ዘፈን አልነበረም ለማለት የሚያዳግም ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልን ስናነብ ስለአይሁድ ባሕል ብዙ ነገር እናገኛለን፡፡ ብሉይና አዲስ ኪዳንን ለመረዳትም ይህንኑ የአይሁድ ባሕል ማጥናት ሊጠቅመን ይችላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር እራሱ በአንድ ዘመን በነበረ ባሕል፣ ቋንቋና ሥልጣኔ አማካኝነት መናገሩን አንዘንጋ፡፡
ወደ አገራችን ስንመጣ እንደ የጉራጌኛ፣ የኦሮምኛ፣ የትግርኛ፣ የአማርኛ፣ የወላይትኛ ወዘተባሕላዊ ጨዋታን በመመልከት ወይም አብሮ በመሳተፍ ላይ ምን ክፋት አለ ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡ በዚያ ውዝዋዜ ከአሥርቱ ትእዛዛት የትኛውን እናፈርሳለን? ከየትኛውስ በደል ሊመደብ ይችላል? ከመግደል ወይስ ከመስረቅ በሐሰት ከመመስከር ወይም ከማመንዘር?
አንዳንድ ጊዜ ሙዚቃና ድምጻዊነት ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ መሆን አለበት የሚል አባባል አለ፡፡ ነገር ግን ቀጥታ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የማይገናኙ ሆኖም ኃጢአት የማንላቸው ብዙ ነገሮችም እንዳሉ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ በቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ይነበባል ለእግዚብሔር ክበር ማለት ነው፤ ታዲያ እኮ በቤታችን የታሪክ ወይም የሳይንስ መጽሕፍትንም እናነባለን፡፡ ንባብ በሙሉ በእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት ብለን ከማንበብ አንታቀብም ወይም ደግሞ በጋዜጣ፣ ታሪክ፣ ስነ-ጸሑፍ፣ የቋንቋ መጻሕፍት ሀጢኃአት ናቸው አንልም፡፡ ግብዣ፣ እሰፖርት፣ የተለያዩ ብሔራዊ በዓላት በቤተክርስቲያን ውስጥ አይከናወኑም፡፡ ነገር ግን ቁምነገር እንዳላቸው አምነን እናከብራቸዋለን እንጅ ኃጢአት ናቸው ብለን አናወግዛቸውም፡፡
ታዲያ ቅዱስ ጳውሎስ የሰው ልጅ ውበትን ጥበብን የሚገልጽበትን ነገር ለምን አወገዘው? እርሱ የተቃወመው እስካሁን እየተነጋገርንበት ያለነውም ሙዚቃ ይሆን? እሱንከመግደል፣ ከስካርና ከቅናት፣ ከመናፍቅነትና ከምቀኝነትጋር እንዴት ሊደምረው ይችላል፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶችም ሆኑ ሌሎች የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በመጀመሪያ የተጻፉት በግሪክ ቋንቋ ስለሆነዘፋኝነትበሚል ቃል የተተረጐመው የትኛው የግሪክ ቃል መሆኑን ማየት ያስፈልጋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በግሪክ ቋንቋ ኮማይ ብሎ ያስቀመጠውም ቃል የአማርኛ መጽሐፈ ቅዱስ /1985 እና 1972 .. ትርጉም/ በዘፋኝነት ይተረጉመዋል፡፡ እርግጥ ቅዱስ ጳውሎስ በሚያወግዘው ድርጊት ውስጥ ዘፈንና ሙዚቃ ይኖራል፡፡ ነገር ግንኮማይየሚለው ቃል ከላይ በተጠቀሰው ዘፈን የሚፈታ አይመስለንም፡፡ኮማይከልቅ ግብረሥጋ ጋር የሚገናኝ ትርጉም አለው፡፡ ሰዎች ለጣዖት አምልኮ እየበሉና እየጠጡ የሚፈፅሙትን ሕገ ወጥ የዝሙት ኃጢአት ያመለክታል፡፡ ይህም በሮማውያንና በግሪካውያን ዘንድ ይፈፀም ነበር፡፡ እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስይህንን የሚፈፅሙ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱምያለበትም ምክንያት አሁን መረዳት እንችላለን፡፡
ለዚህ ተጨማሪ ማረጋገጫ ከፈለግን ብዙ ሰዎችን የእንግሊዘኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን መመልከት እንችላለን፡፡ እንግሊዝኛውኮማይየሚለው ቃል “Orgy” ብሎ ይፈታዋል፡፡ በአንጻሩ በቴሌቪዥን ወይም በሬዲዮ የሚቀርበው ዘፈን “Song” የሚባል ይመስለናል፡፡
በመጨረሻም በአዎንታዊ ትርጉሙ በዘፈን ተፈጥሮን፣ ውበትን፣ፍቅርን፣ መልካም ነገሮችን ማድነቀ እንደምንችል እናውቃለን፡፡ ያን ደግሞ እግዚአብሔር የሚቃወመው አይመስልም፡፡ ስለ ወንድና ሴት ፍቅር መዝፈን ኃጢአት ከሆነመኃልይ ዘሰለሞንየተባለውን መጽሐፍ ምን ልንለው ነው፤ እሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው፡፡ በየትኛውም ደረጃ ብንተረጉመው በቀጥታም ሆነ በተምሳሌነት የወንድና የሴት ፍቅር ይገልጻል፡፡
እንግዲህ አስቀድመን ከመፍረዳችን በፊት ምን ዓይነት ዘፈን ብለን መለየት ያስፈልገናል፡፡ ወደ ኃጢአት ይመራል ወይስ ትምህርታዊ መልእክት አለው? በለን መለየት ያስፈልጋል፡፡ 1879 . የታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ በገላትያ 521 ላይዘፋኝነትተብሎ የተተረጐመውን ቃል ማሶልሶልበሚል ቃል ነው የሚተረጉመው፡፡ ሊፈጠር ከሚችለው የምሥጢር መዛባትና የትርጉም እሻሚነት የሚያድን ቃል ይሆን? ወይስመስከርየሚለው ቃል ከሁሉም ይሻል ይሆን፡፡ ምክንያቱም የግሪኩ ቃል ቅጥ ማጣትንና መስከርን ያሰማልና፡፡ በመሠረቱ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የግዕዙ አዲሰ ኪዳን ገላትያ ምዕራፍ 5 ላይስክረትእንጂዘፈንአይደለም፡፡

የቃላቱን ትርጉም ለማመዛዘን ይረዳን ዘንድ የተለያዩ መዝገበ ቃላት ስለ ዘፈን ወይም ስለመሶልሶል የሚሉትን እንመልከት፡፡
ስለ ዘፈን
የደስታ /ወልድ መዝገበ ቃላት እንዲህ ይላልዘፈን” “ቀነቀነ፣ አወረደ፣ ግጥም ገጠመ፣ አዜመ፣ አንጐራጐረ፣ ዘለለ፣ ተረገረገ
የአማርኛ የመጽሐፍ ቅድስ መዝገበ ቃላት እንዲህ ይላይ (ገጽ. 22-23)
በቅኔና በግጥም ከልዩ ልዩ መሣሪያ ጋር እየተቀነባበረ የሚቀርብ የደስታ ምልክት በልደት ቀን (ኢዮብ 21 11-12 ማቴ. 146) በሠርግ ቀን (ኤር 314 ማቴ.1117) በድል በዓል ቀን (ዘጸ.2ዐ፡21 ምሳ. 1134 1ሳሙ.186) በመንፈሳዊ በዓል ቀን (2ሳሙ. 614) የደረጋል፡፡ ከዚህም ሌላ በልዩ ልዩ የደስታ ቀን ይዘፈናል (ሉቃ. 1525)፡፡ (በእስራኤል የአምልኮት ሥርዓት ዘፈን (ማኀሌት) ትልቅ ቦታ ይይዝ ነበር (መዝ.1493/15ዐ፡4)፡፡ ነገር ግን ባዕድ አምልኮትንና ዝሙትን የሚያስከትል ዘፈን አልተፈቀደም (ዘዳ. 326-19፣ማር. 621-22)፡፡እዚሁ ላይ ሐዋርያት ዘፈን የማይገባ መሆኑን ተናግረዋል ይላል፡፡ ነገር ግን ሐዋርያት ምን ዓይነት ዘፈን እንደተቃወሙ አልገለጹም፡፡ አብዛኛዎቹ ጥቅሶች ተቀባይነት ስላለው ዘፈን እንደገለጹ እናስተውል፡፡
ስለ መሶልሶል
የደስታ /ወልድ መዝገበ ቃላት (ገጽ 118) “ሶለሶለ - አንሶለሶለ፣ አዞር፣ አንቀዠቀዠ፣ አንቀለቀለ መንሶልሶል፣ መዞር፣ መንቀዥቀዥ (መጽሐፍ ግን መሶልሶለ ይላል ገላ. 522)”
የአማርኛ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላትም እንዲህ ይላል፡፡ሶለሶለ - በማያገባ ጥልቅ ማለት፣ በማይሆን ሰዓት በምጣት፣ ሳይጠሩ መምጣት፣ መቀላወጥ፣ የሰው ምግብ ፍለጋ ወዲህና ወዲያ መዞር፡፡
አባ ዳንኤል አሰፋ ዘማኀበረ ካፑቺን - ፍቅርና ሰላም ጋዜጣ ጥር 2003 ዓም።

No comments:

Post a Comment