Tuesday, August 11, 2015

5ቱ የጥምቀት ዓይነቶች

ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና(ዕብ.6፡2)
ጥምቀቶች የሚለው ብዙ ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ በላይ ጥምቀቶች መኖራቸውን ያሳያል፡፡ የሚከተሉትን መዘርዘር ይቻላል፡፡

1.የአካል ጥምቀት

…እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና…
(1ኛ ቆሮ.12፡13)፡፡ አጥማቂ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን መጠመቂያው የክርስቶስ አካል ነው፡፡ …ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን …(ሮሜ.6፡2) ሲል ይህንን ጥምቀት ያመለክታል፡፡ ለመዳን ብቸኛው አስፈላጊ ጥመምቀት ነው ይህ ጥምቀት፡፡ ባመንን ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ አካል ይጨምረናል፤ ኤፌ.1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ ይለናል፡፡ የኤፌ.4፡4-5 ሀሳብ የውሀ ጥምቀት ሳይሆን ይህ ነው፡- አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት የተባለው፡፡

2.የውሀ ጥምቀት

 በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም። እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው? አለው።
ፊልጶስም በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ።
ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም። (የሐዋ.8፡36-38)
አጥማቂው አገልጋይ ሲሆን መጠመቂያው ውሀ ነው፡፡ ይህ ለንሰሐ(ማቴ.3፡11፤ዮሐ.4፡1-2) እና ለበጎ ህሊና ልመና(1ጴጥ.3፡21) ነው፡፡ ምሳሌአዊ አገልጎሎት እንጂ የማዳን ጉልበት የለውም፡፡ ጌታ በዮሐ.3፡5 እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም ያለው ከውሐ መወለድን ከመንፈስ መወለድ ጋር አቆራኝቶ ነው፡፡ ስለዚህ የውሀ ጥምቀት ንሰሐን ያመለክታል፡፡ ማመን ይቀድማል፣ በውሀ መጠመቅ ይቀጥላል፡፡ ለዚህ ነው ማር.16፡16 ያመነ የተጠመቀም ይድናል የሚለን፡፡

በማን ሥም እንጠመቅ?
የተልዕኮ ሥልጣንን በተመለከተ ማቴ.28፡18-19  ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው… ሲለን አጥማቂው አገልጋይ በሥላሴ ሥልጣን ስር ሆኖ እንዲያጠምቅ መታዘዙን ያመለክታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ደግሞ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ…ሲል ተጠማቂው በኢየሱስ ሥም በመማመንና ንሰሐ በመግባት እንደሚጠመቅ ያሳያል፡፡
ስለዚህ በማን ሥም እንጠመቅ ለሚል የ Jesus only አማኞች ጥያቄ መልሱ እንደሚከተለው ይሆናል፡- አጥማቂው የሥላሴን ሥም እየጠራ ያጠምቃል፤ ተጠማቂው ደግሞ የኢየሱስን ሥም እየጠራ ይጠመቃል፡፡ ስለዚህ በማን ሥም እንጠመቅ ለሚለው አብሮ በማን ሥም እናጥምቅ የሚለውም መነሳት አለበት፡፡ ማጥመቅ( βαπτίζοντες ባፕቲዞንተስ) እና መጠመቅ (βαπτισθήτω ባፕቲስዜቶ) የተለያዩ የአንድ ቃል እርባታዎች ናቸው፡፡

3. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት

ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ (የሐዋ.1፡5)
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ (የሐዋ.1፡8)
እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል (ማቴ.3፡11)
አጥማቂው ኢየሱስ ሲሆን መጠመቂያው መንፈስ ቅዱስ  ነው፡፡ አስፈላጊነቱ ለአገልግሎት ኀይልና የተለያዩ ፀጋ ስጦታዎችን ለመቀበል ነው፡፡ በበዓለኀምሳ ቀንም የሆነው አስረጂ ነው፡፡ በውሐ ዕንዲጠመቁ የተነገራቸውም ይህንን ስጦታ ማግኘት እንደሚችሉ የዘር ዘራቸው እና በሩቅ ያሉም የዚሁ እድል ተጠቃሚ ዕንደሚሆኑ የተነገራቸው እንዲህ በማለት ነው፡-  
የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና (የሐዋ.2፡38-39)፡፡ 1ኛ ቆሮ. 12 የሚከተለውን ይለናል፡-
7 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።
8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥
9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥
10 ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
11 ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።

4. የእሳት ጥምቀት

እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል (ዮሐ.3፡11)፡፡
ሁለት የተለያዩ ጥምቀቶች ናቸው የተጠቀሱት፡፡ የመንፈስ ጥምቀትን ተነጋግረንበታል፡፡ አብሮ የተጠቀሰው የእሳት ጥምቀት ነው፡፡ አጥማቂው ጌታ ነው፤ መጠመቂያው ደግሞ መንፈሳዊ እሳት፡፡ አስፈላጊነቱን በተመለከተ ቀጥር 12 ላይ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል ይለናል፡፡ ህይወትን የሚያጠራ እሳት ነው፡፡ በሚልክያስ መጽሐፍ መዕራፍ 3 ላይ ጥሩ ትንቢታዊ ማስረጃ አለን፡-
1፤ እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
2፤ ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?
3፤ እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።
4፤ እግዚአብሔርም እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ቍርባን ደስ ይለዋል፡፡
                 
5. የመከራ ጥምቀት

 ኢየሱስም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ ሲል ለዘብዴዎስ ለጆች የተናገረው ነው (ማር.10፡39)፡፡

አጥማቂ አልተጠቀሰም፡፡ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ መጠመቂያው መከራ ነው፡፡  አስፈላጊነቱ ለብስለት (ያዕ.1፡2-4) ወይም በጥበብ ለማደግ እና መታዘዝን ለመማር (ያዕ.1፡5፤ዕብ.5፡8-9፤ሉቃ.2፡52) እንዲሁም ለባህሪ መታነጽ ነው(ሮሜ.5፡3-4)፡፡

http://restorers.page.tl/%26%234768%3B%26%234637%3B%26%234661%3B%26%234725%3B-%26%234768%3B%26%234845%3B%26%234752%3B%26%234725%3B-%26%234901%3B%26%234637%3B%26%234672%3B%26%234726%3B%26%234733%3B.htm

Sunday, August 2, 2015

በሮሜ8፡-34 ላይ የተጣለው ማዕቀብ እስከ መቼ ይሆን የሚዘልቀው??

ተዋዳጆች ሆይ፡- ሐዋያው ጳውሎስ ሮሜ8፡-34ን ‹‹ስለኛ የሚማልደው›› ብሎ እንጅ ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ሲል አለመጻፉን የጥንቷም ትሁን የዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታውቃለች!! እራሷም ትመሰከራለች!! በ2000 ዓ/ም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለራሷ ባሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካለምንም ምክንያት፤ በድፍረት ብቻ ‹‹ስለእኛ የሚማልደው›› የሚለውን ሐዋርያዊ ቃል በመሻር ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ተብሎ ተቀይሮአል፡፡ ታዲያ ማዕቀብ መጣሉ ለምን አስፈለገ?? ሐዋርያው የተጠቀመው ሐረግ ‹‹ስለእኛ የሚማልደው›› በማለት እንደሆነ እንጅ ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› አለማለቱን፤ የግሪኩን መጽሐፍ ተመልክተን የጥንቷም ትሁን የዘመኗ ኦረቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይሄን እንደምታውቅ በአራት ማስረጃዎች እንገልጣለን፡-
1ኛ== ሁሉም እንደሚያውቀው ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፉት በግሪክ ቋንቋ ነው፡፡ በመሆኑም ዋናው ቁምነገር ያለው ይሄን ቃል ሐዋርያው በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምን ሲል እንደጻፈልን በሚገባ ማየቱ ላይ ስለሆነ በ“strong’s Hebrew And Greek dictionary” ላይ በማመሳከር የተቀመጠውን ቃል እንመልከት፡-
Rom 8፡-34 ‹‹Who is he that condemneth? It is Christ that died, yea rather, that is risen again, who is even at the right hand of God, who also maketh “INTERCESSION” for us.›› KJV. በአማርኛችን <<የሚማልደው>> በሚለው ቃል የተጻፈው፤ በኢንግሊዘኛው ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ <<INTERCESSION>> የሚለውን አቻ ቃል የያዘ ነው፡፡
Rom 8፡-34 ‹‹Who<3588><3588><5101> is | he that condemneth<2632>? It is | Christ<5547> | that died<599>, | yea<1161> | rather<3123>, | that is risen<1453> | again<2532>, | who<3739> | is<2076> | even<2532> | at<1722> | the right hand<1188> | of God<3588><2316>, | who<3739> | also<2532> | maketh “INTERCESSION <1793>” | for<5228> | us<2257>. |›› በዚህም መሰረት <<INTERCESSION>> የሚለው ቃል ወደ “strong’s Hebrew And Greek dictionary” የማመሳከሪያ ኮዶች ስናየው በቁጥር “INTERCESSION <1793>” ላይ የተመለከተው ሲሆን፤ ይሄን በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ቃል ወደ ኢንግሊዘኛ ሲፈታው እንዲህ የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠን፡-
<<1793 entugchano, en-toong-khan'-o>>:- deal with, make intercession.>> በዚህ መሰረት በግሪኩ ሐዋርያው ‹‹deal with, make intercession.›› የሚል ፍቺ ያለው ቃል የተጠቀመ ሲሆን ትርጉሙን ወደ አማርኛችን ስናመጣው ‹‹ማስማማት/ማስታረቅ/፣ ማማለድ/ምልጃ/›› የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠን እንጅ ስለ ፍርድ የሚያወራ አንዳችም ቃል ይቅርና የሚያስጠረጥርም ነገር አልተጠቀመም፡፡ ደግሞም በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ‹‹የሚፈርደው›› የሚለውን ቃል ሐዋርያቱ ምን የሚል ቃል እንደተጠቀሙ ማየቱ ነገሩን በይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ በዚህም መሰረት ‹‹የሚፈርደው›› የሚለውን ቃል በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን 1ጴጥ1፡-17 ላይ ‹‹ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው ==የሚፈርደውን== አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።›› የሚል እናገኛለን፡፡ ከዚህ ተነስተን ‹‹የሚፈርደውን›› ለሚለው ቃል በ“strong’s Hebrew And Greek dictionary” ላይ ስናመሳክረው፤ በኢንግሊዘኛው //judgeth// ለተባለው ቃል የግሪኩን አቻ ቃል በኮድ ቁጥር “2919” ላይ የተመለከተው ሲሆን፤ ቃሉም፡- <<krino, kree'-no>> የሚል ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ ሮሜ8፡-34ን በግሪኩ //የሚፈርደው// ብሎ ጽፎ ቢሆን ኖሮ፤ መጠቀም የነበረበት ‹‹krino, kree'-no›› የሚለውን ቃል እንጅ፤ //የሚማልደው// የሚለውን ‹‹entugchano, en-toong-khan'-o›› ቃል መጠቀም አልነበረበትም፡፡ ተዋዳጆች ሆይ፡- ታዲያ የሐዋርያውን ቃል ሽሮ፣ ሐዋርያቱ ያላስተማሩንን፣ እኛም ከቶ በማናውቀው፣ ጌታ መንፈስ ቅዱስ የማይከብርበትን፣ //የሚፈርደው// በተባለ እንግዳ ቃል፣ ማዕቀብ መጣሉ ለምን ያስፈለገ ይመስላችሃል??
2ኛ== የጥንቷ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈውን ‹‹ስለእኛ የሚማልደው›› ብላ እንደምታምን ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ይሄን በዕብ7፡-25 ‹‹ሊያማልድ›› ብሎ ሐዋርያው እንደጻፈ እንጂ ‹‹ሊፈርድ›› ብሎ እንዳልጻፈ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በድረሳኑ ላይ ሲያብራራ በግልጽ አስቀምጦታል አልነበረም፡-
#‹‹እመሰኬ ካህን ውእቱ አሜሃ ይተንብል፤ ወዘይቤሂ ጳውሎስ ይተንብል በእንቲአነ ዝኒ እስመ ሊቀ ካህናት ይተንብል፡፡ ወጊዜ ፈቀደ ይተንብል ሎሙ፤ ወአኮ በዝንቱ ጊዜ ባህቲቱ፤ አላ በእንተ ዘትመጽእ ሕይወት ዘለዓለም››
‪#‎በአማርኛ‬ ሲተረጎም፡- ‹‹መለመኑ መማለዱ ሊቀ ካህናት ቢሆን እኮ ነው፡፡ ጳውሎስ ስለኛ **ይለምናል፣ ይማልዳል** ያለው የሊቀ ካህንነት ሥራ መለመን መማለድ በመሆኑ ነው፡፡ በወደደበት ጊዜ **ይለምናል ይማልዳል የሚለምነው የሚማልደው** በአሁኑ ጊዜ ብቻ አይደለም፤ ስለምትመጣውም ስለዘላለማዊት ሕይወትም **ይለምናል ይማልዳል** እንጅ፡፡›› ድርሳነ ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ 13ኛው ድርሳን ይመልከቱ፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡- ታዲያ ትውልድን ሁሉ የሚገድለው የዚህ አደገኛ ኑፋቄ ምንጩ ከወዴት ነው ትላላችሁ??
3ኛ== በ2000ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ያሳተመችው፤ የግዕዙን መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ተደርጎ ነው የተተረጎመ በማለት ሲሆን፤ የግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሚደግፋት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የግዕዙ መጽሐፍ ይሄን ሐረግ የተጠቀመው፡- “ይትዋቀሥ በእንቲኣነ” በሚል ሲሆን፤ ወደ አማርኛ በቀጥታ ሲተረጎም፡- “ስለ እኛ ይሟገታል ወይም ይከራከራል” የሚል ፍቺ ነው የሚሰጠው እንጅ ስለፍርድ የሚያወራ አይደለም፡፡ ለዚህ ማስረጃ የምናደርገው ቤተክርስቲያኒቱ የምትጠቀምበት ‹‹መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት›› የሚሰጠውን ፍች በማሳየት ይሆናል፡፡ “ተዋቀሠ” የሚለውን የግዕዙን ግስ ሲተረጎም፡- //በቁሙ (ተዋቀሠ)፣ ተሟገተ፣ ተከራከረ// የሚል ፍች ነው ያስቀመጠው እንጅ፤ ጭራሽ “የሚፈርደው” በማለት አልተረጎመውም (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ 401 ላይ ይመልከቱ)፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡- ታዲያ እያወቁ እንዳላወቁ በማስመሰል እንዲህ አይነት ክህደት በሕዝቡ ላይ መጫን ለምን ያስፈለገ ይመስላቹሃል??
4ኛ== ሌላውና በጣም የሚያሳዝነው ይህችው የዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለራሷ አስተምህሮ ስትል እየተንገዳገደ መድረሻውን ላጣው የስህተት ትምህርቷ ይደግፈኛል ብላ ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ስትል ብትተረጉመውም፤ በዚሁ በ2000ዓ/ም በታተመው መጽሐፍ ላይ ይሄን ሮሜ8፡-34 ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ያሉትን ቃል ለማብራራት፤ በግርጌ መግለጫ ላይ ያስቀመጠችው ‹‹//ግሪኩ ‹‹የሚማልደው›› ይላል//›› በማለት ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡- ታዲያ ይሄን መንፈሳዊ እውርነት ምን ትሉታላችሁ?? ዓይናቸው እያየች፣ ጆሮቸውም እየሰማች፣ የሐዋርያውን ቃል በመሻር ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ብሎ መጻፍ ምን የሚሉት ቅዠት ነው?? የሰው ልጅ የልቡ መደንደን በኃይል ሲበረታ፣ እራሱ ለፈጠራት አስተምህሮ፣ የአምላኩን ቃል ይሽራል፡፡ ለዚህ መልዕክት በማስረጃነት በተለቀቀው ፎቶ ላይ መመልከትና ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ታዲያ የህችን ቤተክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልግሻል ስትባል ልቧን አደንድና አያስፈልገኝ ስትል መስማት ምን ያህል ያሳፍራል!! ተሃድሶ ማለት ወደ ቀደመ መልክና ውበት ወደ ትክክለኛ ማንነት መመለስ፤ ከእንዲህ አይነቱ ከሳቱበትና ከጠፉበት የስህተተት ጎዳና በንስሃ ወደ አምላክ ሃሳብና ፈቃድ በመመለስ ሁሉን ቻዩ ለሆነው ጌታ ሁለተናን ማስገዛት ነው፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን፡- እግዚአብሔር ስለ ልጁ ኢየሱስ ሲል ምህረቱን ያብዛልን!! በምስኪኑ ሕዝብ ላይ የታወጀው ግፍ በጣም የሚያሳዝን፣ ልብም የሚያደማ፣ ማቅ የሚያስለብስ በንስሃ የሚያስጮኽ አረመኒየያዊ ድርጊት ነው፡፡
‪#‎ተወዳጆች‬ ሆይ:- ሕሊናችሁ ለእውነት የሚወግንላችሁ ብቻ ልጠይቃችሁ እስቲ፣ ይሄ ማዕቀብ ምንድን ነው ትላላችሁ?? መርዘኛ የሆነውን የዲያብሎስን የጨለማ ሃሳቡንና ፈቃዱን፣ የምስኪኑን ሕዝብ ልብ አሳውሮ ወደ ሲኦል የሚነዳውን አደገኛ ግብሩን አታስተውሉምን?? የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስ ተገለጠ ተብሎ እንደተጻፈ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሄ ትውልድ ገዳይ ሥራው የፈረሰ የፈራረሰ ይሁን!! አሜን!! የተሃድሶ አገልግሎት ይሄን አደገኛ ኑፋቄ የታወጀበትንና የተበረዘውን ቃል ወደ ቀደመውና እውነተኛ ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል ተመልሶ ይተካ ዘንድ አንዱ ብርቱ ትግሉ ነው፡፡ ኢየሱስ እንጅ ማን ያሸንፋል?? አሜን በእግዚአብሔር ቃል ይተካል! 

ተሃድሶ ለኦርቶዶክስ!

ጵራቅሊጦስ በሚለው ቃል የተሰራው “ግፍ” ሲገለጥ፡-

          <<ጵራቅሊጦስ>> በሚለው ቃል የተሰራው “ግፍ” ሲገለጥ፡-

    በ2000 ዓ/ም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ያሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ በ1ዮሐ2፡-1 ላይ ያለውን ቃል እንዲህ በማለት ነው የተጻፈው፡-
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡-1 “ልጆቼ ሆይ፥ እንዳትበድሉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። የሚበድልም ቢኖር ከአብ ዘንድ <<ጵራቅሊጦስ>> አለን፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢያታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ ጻድቅ ነው፡፡” <<ጠበቃ>> የሚለውን የአማርኛ ቃል ቀይረው በምትኩ ደግሞ የግሪኩን ቃል <<ጵራቅሊጦስ>> //parakletos// የሚለውን ተጠቅመዋል፡፡ በግርጌ መግለጫው ላይ ያሰፈሩትም <<የግሪኩ፡- ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ “ጵራቅሊጦስ” አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።>> በማለት ብቻ ነው ያስቀመጡት፡፡ በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የምስኪኑን ሕዝብ ማዕከል ያደረጉ 2 የተፈጸሙ አበይት ስህተቶች እንመልከት፡-
1ኛ/ የመጀመርያው ስህተቱ “ጵራቅሊጦስ” የሚለው ቃል “ገላጭነቱ” ወይም “አስረጅነቱ” ለኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ሳለ በመቀየር ለመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተደርጎ መጻፉ ነው፡፡ ይህም “ጵራቅሊጦስ” የሚለው ቃል መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በቤተክርስቲያኒቱ ስር የሰደደ ትምህርት ከመኖሩ ጋር በማያያዝ፤ ከአብ ዘንዳ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው የሚል ድምዳሜን በመስጠታቸው ነውና፤ የክርስቶስን ዘላለማዊ የሊቀ ካህንነቱን አገልግሎት ለመሸፈን የተደረገ ስልታዊ ኑፋቄ ነው፡፡ ነገር ግን “ጵራቅሊጦስ” የሚለው የግሪኩ ቃል ሕይወት ያለው የአካላዊው መንፈስ ቅዱስ የስም መጠሪያ ሆኖ ሳይሆን የተጻፈው፤ ይልቁንም <=== የመንፈስ ቅዱስን የሥራ ድርሻ ወይም በክርስቶስ የሆኑትን አማኞች በሙሉ የሚያጽናና መሆኑን===> የሚገልጥ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በአማርኛ <<አጽናኝ፣ ጠበቃ፣ አማላጅ፣ ወኪል>> እንደማለት ማለት ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ቃል በ“strong’s Hebrew And Greek dictionary” ላይ በማመሳከር ማየት ይሆናል፡-
1John 2፡-1 “My little children, these things write I unto you, that ye sin not. And if any man sin, we have an <<ADVOCATE>> with the Father, Jesus Christ the righteous” KJV. በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ <<ጵራቅሊጦስ>> የሚለው ቃል በኢንግሊዘኛው <<ADVOCATE>> የሚለውን አቻ ቃል የያዘ ነው፡፡
1John 2፡-1 “ My<3450> | little children<5040>, | these things<5023> | write I<1125> | unto you<5213>, | that<2443> | ye sin<264> | not<3361>. | And<2532> | if<1437> | any man<5100> | sin<264>, | we have<2192> | an advocate<3875> | with<4314> | the Father<3588><3962>, | Jesus<2424> | Christ<5547> | the righteous<1342>” በዚህም መሰረት
<<ADVOCATE>> የሚለው ቃል ወደ “strong’s Hebrew And Greek dictionary” የማመሳከሪያ ኮዶች ስናይ በቁጥር “an advocate<3875>” የተመለከተው ሲሆን፤ በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ጵራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ሲተረጉም እንዲህ የሚል ትርጉም አለው፡-
=== <<3875 parakletos, par-ak'-lay-tos>> “AN INTERCESSOR, CONSOLER, ADVOCATE , COMFORTER” የሚል የቃል ፍቺ ነው የሚሰጠው፡፡ በዚህም መሰረት “ጵራቅሊጦስ” የሚለው ቃል <<አማላጅ፣ ጠበቃ፣ አጽናኝ፣ ወኪል>> ማለት ነው እንጅ የአካላዊው መንፈስ ቅዱስ የስም መጠሪያው አይደለም፡፡ ሙሉ በሆነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ ጌታ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንደርሱ ያለ ሌላ አጽናኝ ከእነርሱ ጋር እንዲኖር ወደ አባቱ እንደሚጸልይ በገለጠ ጊዜ፤ “አጽናኝ” ወይም በግሪኩ “ጵራቅሊጦስ” የሚለውን ቃል “የአካላዊውን የመንፈስ ቅዱስ” ስም መጠሪያ እንደሆነ አድርጎ ሳይሆን የተጠቀመበት፤ ይልቁንም ደቀመዛሙርቱን የሚያበረታ፣ የሚያጽናና፣ የሚደግፍ፣ ከአብ ዘንድ እንደሚመጣና በተስፋ እንዲጠብቁ የሚያበረታታ ቃል አድርጎ መናገሩን ማስተዋል ከበቂ በላይ ነው፡- በዮሐ14፡-15/16 “ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር “ሌላ” <<አጽናኝ>> ይሰጣችኋል፡፡” ሌላው በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ===የአካላዊው መንፈስ ቅዱስ=== የስም መጠሪያን ማውቁ ያስፈልጋል፣ ይህም በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን ማቴ28፡-19 ላይ <<መንፈስ ቅዱስ>> ብለን እንደምንጠራው በግሪኩ ደግሞ በ“strong’s Hebrew And Greek dictionary” ስናመሳክረው “4151 pneuma, pnyoo'-mah” የሚል የስም መጠሪያ ነው ያለው፤ እንጅ “parakletos” አለማለቱን ልብ ይሏል፡፡ እንግዲህ በግልጥ እንዳየነው “ጵራቅሊጦስ” የሚለው ቃል የኢየሱስንና መንፈስ ቅዱስን ሥራ/ግብር/ የሚገልጥ ገላጭ ቃል (በዮሐ14፡-15/16) እንጅ የመንፈስ ቅዱስ የመጠሪያ ስም አይደለም፡፡ በመሆኑም በ1ዮሐንስ መልዕክት 2፡-1 ላይ ያለው ቃል ስለ መንፈስ ቅዱስ አንዳች የሚያወራ ሃሳብም ይሁን ዘይቤ ሊኖረው ይቅርና የሚያስጠረጥርም ነገር የለውም፡፡ የዮሐንስ መልዕክት አውዳዊ ሃሳብ ሙሉ በሙሉ የሚያመለክተውና የሚያውጀው ክርስቶስ ኢየሱስን ብቻ ነው፡፡
2ኛ/ ሁለተኛው ስህተት “ጵራቅሊጦስ” የሚለውን ቃል በቀጥታ ከግሪኩ ወስደው ለመጽሐፉ ሲጠቀሙ በግርጌ መግለጫ ላይ፤ ቃሉን ካለምንም ትርጉምና <<የአማርኛ አቻውን ቃል>> ለምን ሳይጠቀሙ እንደቀሩ፤ ምንም ዓይነት ማብራሪያ ሳይሰጡ የማለፋቸው ምስጢር ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው ሐዋርያቱ አዲስ ኪዳንን በጻፉት የግሪኩም ይሁን በኢንግሊዘኛው KJV እንደገናም ደግሞ በ1954 ዓ/ም የታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዳረጋገጡልን “ጵራቅሊጦስ” የሚለው ቃል <<አማላጅ፣ ጠበቃ፣ አጽናኝ፣ ወኪል>> ማለት እንደሆነ አይተናል፡፡ በ2000ዓ/ም ላይ በታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ጵራቅሊጦስ” ለሚለው የግሪኩ ቃል የአማርኛ አቻ ቃሉን እንደአውዱ ሲተረጎም <<ጠበቃ>> የሚለው ቃል ሊቀመጥ እንሚገባ አጠውት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት መጽሐፍ ላይ “ጵራቅሊጦስ” የሚለውን የግሪኩን ቃል ሁለት ፍቺ የሰጡት ሲሆን፣ የመጀመርያው፡- <<አማላጅ፣ አስታራቂ፣ አፍ፣ ጠበቃ፣ ትርጁማን፣ አምጃር፣ እያጣፈጠ የሚናገር፣ ስብቅል ከአፉ ማር ጠብ የማይል>> በማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፡- <<ናዛዚ መጽንኢ፣ መስተፍሥሒ፣ መንፈስ ቅዱስ፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ ትንሳኤ ዐምሳኛ፣ የዕርገት ዐሥረኛ፣ እሁድ ቀን የሚውል>> የሚል ነው፣ መዝገበ ቃላት (1948// 907) ላይ ይመልከቱ፡፡ በ1ዮሐ2፡-1 በግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንዲህ ነው፡-
“ደቂቅየ ዘንተ እጽሕፍ ለክሙ ከመ ኢትአብሱ ወእመኒ ቦ ዘአበሰ <<ጵራቅሊጦስ>> ብነ ኀበ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ ውእቱ ይኅድግ ለነ ኃጣውኢነ ወአኮ በእንቲኣነ ባህቲቱ አላ በእንተ ዓማኒ”
ለዚህም ቃል የአማርኛ ትርጉም የተሰጠው እንዲህ የሚል ነው፡- “ልጆቼ ሆይ፥ እንዳትበድሉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። የሚበድልም ቢኖር ከአብ ዘንድ <<ጵራቅሊጦስ>> አለን፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢያታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ ጻድቅ ነው፡፡” እኝህ ሊቅ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “ወእመኒ ቦ ዘአበሰ <<ጵራቅሊጦስ>> ብነ ኀበ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ” ለሚለው የግዕዝ መጽሐፍ ወደ አማርኛ ሲያመጡ የሰጡት አቻ ቃል ከላይ እንዳየነው የመጀመርያውን ትርጉም ነው፡፡ ይሄውም <<አማላጅ፣ አስታራቂ፣ አፍ፣ “ጠበቃ”፣ ትርጁማን፣ አምጃር፣ እያጣፈጠ የሚናገር፣ ስብቅል ከአፉ ማር ጠብ የማይል>> የሚለውን ትርጉም ነው፡፡ በመሆኑም <<ጵራቅሊጦስ>> የሚለው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን እንጅ መንፈስ ቅዱስን እንደማያመለክት ገልጠዋል፡፡ በ1954 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ እትም <<ጵራቅሊጦስ>> የሚለውን የግሪክ ቃል በአማርኛ አቻ ቃሉ <<ጠበቃ>> መባሉ ምን ያህል ትክክል እንደሆነ ማወቅ በቀላሉ እንችላለን፡፡
ወዳጆቼ በእነዚህ ሁለት አበይት ስህተቶች የደረሰው ነገር በሕዝቡ ላይ ሞት ብቻ ነው፡፡ የክርስቶስን ዘለዓለማዊ የሆነውን የሊቀ ካህንነት ሥራ ክዶ ጽድቅ የሚባል ነገር የለምና፡፡ ታዲያ ለምን ይሄን አይነት ክህደት መፈጸሙ አስፈለ ስንል፡- በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያሉ የክርስቶስ ወንጌል ተቃዋሚዎች፣ የክርስቶስን ዘላለማዊ የሊቀ ካህንነት አገልግሎት ክደው ምስኪኑን ህዝብ ለማስካድ ምንም አይነት ርህራሄ የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡ ለምስኪኑ ህዝብ ምንም አይነት ኃላፊነት የማይሰማቸው፣ <<በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሞት ደብዳቤ የሚጽፉ>> ለዲያብሎስ ሃሳብ የወገኑና ልባቸውን ለድቅድቅ ጨለማ ያስማረኩ ሐኬተኞች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በጨለማ ለሚወነባበደው፣ ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ለሚቅበዘበዘው ምስኪን ሕዝብ፣ እውነቱን እየገለጠለት ከዘለዓለማዊው ሞት ያመልጥ ዘንድ፣ እኛ ግን የክርስቶስ ሕይወት እጅግ በዝቶ የተትረፈረፈልን ክርስቲያኖች በብርቱ እንጸልያለን፡፡
ተሐድሶ ለአርቶዶክስ!!
https://www.facebook.com/groups/705796459440764/permalink/967146109972463/ 

ድርብ ታቦት ከየት መጣ? ተሸክሞ መዞርስ ለምን አስፈለገ?

ድርብ ታቦት ተብሎ መታወቅ የጀመረው በግራኝ መሐመድ ዘመን ነው ይባላል። ግራኝ መሐመድ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያቃጥል ቀሳውስት ታቦቱን እያሸሹ ወደአልተቃጠለ ቤተ ክርስቲያን እየወሰዱ ይደርቡ ነበር፣ አንዳድ ታቦቶች ሌላ ቤት ተሥርቶላቸው የተመለሱ ሲሆን አንዳዶች ግን በዚያው ተደረበው ቀርተዋል። ዛሬ በአንዳድ አብያተ ክርስቲያናት ከ40 በላይ ታቦቶች (የምሥክር ወረቀቶች)የመገኘታቸው ምክንያት ይኸው ነው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን አንዳድ የጥቅም ደብተራዎች ድርብ ታቦትን የቢዝነስ ሥራ አደረጉት።
ድርብ ታቦት አሁን አሁን የቢዝነስ ጉዳይ ብቻ ነው። የሥጋውና ደሙ መሠዊያ ነው ብለው የሚሰብኩትን አያወጣቸውም። ምክንያቱም ሥጋና ደሙ የሚሠራው በአንድ ታቦት ብቻ ነውና መደራረቡ ለምን አስፈለገ? እንላለን። እኛ ድርብ ታቦት የገንዘብ ማግኛ ዘዴ ነው ያልበንትን ምክንያት ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር እናቅርብ።
ለምሳሌ፤ ጎላ ሚካኤል ድሮ ሚካኤል ከመደረቡ በፊት የመንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ነበር። በኋላ ግን ሕዝቡ መንፈስ ቅዱስን ባለማወቁ ወደዚያ ሊመጣና ገንዘብ ሊሰጥ ባለመቻሉ ሕዝቡ የለመደው ሚካኤል ተደረበ፣ ከዚያም ሕዝቡ መምጣትና ገንዘቡን ማዝነብ ሲጀምር ሚካኤል ከመንፈስ ቅዱስ መብለጡን ለማሳየት "ጎላ” ሚካኤል ተባለ። ጎላ ሚካኤል የመንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የነበረ መሆኑን እስካሁን ድረስ "ጽርሐ ጽዮን” እየተባለ መጠራቱን ልብ ይበሉ።
ቀጨኔ መድኃኔ ዓለም ከጥንት ጀምሮ በመድኃኔ ዓለም የተሰየመ ነበር። ሕዝቡን መድኃኔ ዓለምን ባለማወቁና ገንዘብ ሊገኝ ባለመቻሉ ገብርኤል ተደረበ በሩ አካባቢም ትንሽ ቤተ መቅደስ ተሠርቶለት ትልቅ የገቢ ምንጭ ሆኗል። ሕዝባችን ከመድኃኔ ዓለም ይልቅ ገብርኤልን የሚያመልክ መሆኑ የታወቀ ነው። በነገራችን ላይ እስከዚህ ዘመን ድረስ በሌላ ታቦት ላይ ሲደረቡ የኖሩት ሦስቱ ታቦቶች ናቸው እነርሱም ማርያም፣ ሚካኤል፣ ገብርኤል ሲሆኑ አሁን አሁን ግን አርሴማና የሸንኮራው የሐንስ በብዛት እየተደረቡ ነው። እስከ ዛሬ በገብርኤል፣ በሚካኤል፣ በማርያም ላይ የተድረበባቸው ታቦት የለም እነርሱ ግን በሌላ ታቦት ላይ እየሄዱ መደረብን ይዘውታል። ተክለ ሃይማኖትና አቡነ አረጋዊ አስካሁን ተከባብረው ይኖሩ ነበር ማለት አንዱ ባንዱ ላይ አይደረብም ነበር አሁን በአሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ተደራርበው እየኖሩ ነው። በተክለ ሃይማኖት ሽዋዎችን በአቡነ አረጋዊ ትግሬዎችን ለመያዝ ተብሎ የተደረገ ነው።
ድሮ ድሮ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድን የሚያመልከው አልነበረም በሸንኮራ እስኪታወቅ ድረስ። ለምሳሌ ጎጃም በረንዳ አካባቢ ያለው ወልደ ነጎድጓድ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እውቅና በማጣቱ ገንዝብ ሊገኝ አልቻለም ነበር በኋላ ግን ማርያም ተደርባ ትልቅ የገቢ ምንጭ ፈጥራለች፣ እዚያው አንድ ግቢ ውስጥ ሁለት ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ ጥሩ ገቢ ተገኝቷል። በጎጃም በረንዳ አልታወቅ ብሎ የነበረው ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፤ ሕዝቡ እስካሁን ባልለመደው በቦሌ መድኃኔ ዓለም ላይ ተደርቦ የካህናቱን ደሞዝ በሚገባ እየሰበሰበ ነው። በነገራችን ላይ ሕዝቡ ዮሐንስ መሆኑን እንጂ መጥምቁ ይሁን ወንጌላዊው ለይቶ አያውቅም፣ ብቻ ዮሐንስ ይሁን፣ ይህን እውቅና ያገኘውም በሸንኮራ ያድናል ስለተባለ ነው። በአሁኑ ሰዓት አርሴማ ሁሉንም እየቀደመች በብዙ ቦታ እየተደረበች ነው። እርሷ የወጣቱ አምላክ ሆናለችና ካህናቱም ቢዝነስ እየሠሩባት ነው።
ዛሬ በአዲስ አበባ ከ50 በላይ የተደራረበ የገብርኤልና የማርያም ቤተ ክርስቲያን ሲኖር የኢየሱስ ግን ሁለት ብቻ ናቸው ገነተ ኢየሱስና ገዳመ ኢየሱስ። ገነተ ኢየሱስ ገንዝብ ባለማምጣቱ ማርያም ተደርባለች አንድ ግቢ ውስጥ፡ሁለት ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል። ስለዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ አንድ ብቻ ይሆናል እርሱም ገዳመ ኢየሱስ ነው። እርሱስ የሰው ልጅ ግን እራሱን የሚያስጠጋበት የለውም ያለው ለዚህ አይደል?
ማጠቃለያ
እውነተኛው ታቦት የፈቃድ ወረቀት ስለሆነ በክብር መያዛችን አይከፋም ስጋውና ደሙን ብንሰዋበትም አይጎዳንም። ተሸክመነው የምንዞርበት ምክንያት ግን አይታወቅም፣ ለፌስቲባል ወይም ለባህል ድምቀት ከሆነ ጥሩነው፤ ለስግደትና ለአምልኮ ከሆነ ግን ትልቅ ስሕተት ነው ለማን ነው የምንሰግደው? ለምሳሌ ታቦቱ የሚካኤል ከሆነ ለሚካኤል መስገዳችን ነው ያርሴማም ከሆነ እንዲሁ? የሚካኤልና የሥላሴ ታቦት አንድ ላይ ቢወጡ ለማን ነው የምንሰግደው? ለሁለቱም የሚል መልስ ሊኖር ይችላል ሁለቱን ባንድ ጊዜ ማምለካችን ነው ማለት ነው? ለሚካኤል የምንሰግደውና ለሥላሴ የምሰግደው በምን ይለያል? እኛ ይህን ጥያቄ ያነሳነው ለማን መስገድ እንዳለብን ስለማናውቅ አይደለም ሰማይና ምድርን ለፈጠረው በሁሉ ለሚገኘውና ለተፈራው አምላክ ብቻ በመንፈስ እንሰግዳለን ለሌላ ለማንም አንሰግድም ዮሐ 4፥21-26 "እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልስጥም‚ኢሳ 42፥8 ይላልና እኛም ለማንም አንሰጥም።
ድርብ ታቦት ለገንዘብ ነው ሌላ ምንም ምስጢር የለውም፣ ይህ የዘረፋ ስልት መቆም አለበት፣ ያታለልንበት ዘመን ያበቃ ይመስለናል፣ ሰውን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርንም ንቀናል ስለዚህ እግዚአብሔር ለክብሩ ተነሥቷል ሕዝባችንን ያዋረደውን ሁሉ ከንቱ ነገር እራቁቱን ሊያስቀረው ለሐፍረትና ለመሳቂያ ሊያደርገው ተነሥቷል። የሚመጣው ትውልድ የሚታለል አይደለምና ከወዲሁ እንንቃ።
የገንዘብ ጉዳይ ከሃይማኖት ጋር በመያያዙ ባዕድ አምልኮዎች ተስፋፍተዋል፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለሆኑ ልማዶችም ሕዝቡን አንቀው በመያዛቸው በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በመንፈሳዊ ሕይወቱ ነጻ መውጣት አልቻለም፣ የሀገሪቱ ችግር የሃይማኖት ችግር ነው፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለሆነ፣ ኦርቶዶክሳዊም ያልሆነ፣ የሩቅ ምሥራቅ አገሮች ልማድ ሥራ አስፈትቶን አደንዝዞንና አስንፎን ይገኛል። ይህ ተጠራርጎ መወገድ አለበት፣ ዘመኑ የተሐድሶ ነውና እንታደስ።

የኢትዮጵያ ታቦት፤ ታቦትም ካልሆነ ጽላትም ካልሆነ ምን እንበለው ይሆን?


ታቦት ማለት ጽላት የሚቀመጥበት ሳጥን ማለት ነው ጥሬ ትርጉሙ ማደሪያ የሚል ነው የጽላት ማደሪያ ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ ታቦት የሚለው ምን ዓይነት እንደሆነ ዘጸ. 25፥10-22 የተጻፈውን መረጃ በማድረግ ምስሉን ጨምር እናሳያችሁ። ከላይ በጠቀስነው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ታቦት ከግራር እንጨት የሚሠራና በወርቅ የተለበጠ ትልቅ እቃ ነው።
1. ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣
ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል፣
ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል ነው።
ታቦቱ አንድ ብቻ ነው
2. በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ፣
ዙሪያውን የወርቅ አክሊል ያለው፣
አራት እግሮች ያሉት
አራት ቀለበቶች ያሉት
ሁለት መሎጊያዎች(መሸከሚያዎች)ያሉት ነው።
3. በላዩ ላይ ሁለት ክንድ ተኩል የሆነ የሥርየት መክደኛ ያለው፣
በላይና በታች በዚህና በዚያ ሁለት ኪሮቤል ያለው፣
ስያሜው የቃል ኪዳኑ ታቦት ተብሎ ይጠራል።
ጽላት
አሠርቱ ትእዛዛት በሁለት ወገን የተጻፉባቸው ሁለት ድንጋዮች ናቸው፤ ሁለቱም ጽላቶች ከላይ በተገለጠው ታቦት ውስጥ ይቀመጣሉ። ከቶ ከዚያ አይወጡም። ዘጸ 32፥15
አገልግሎቱ
ሁለቱን ድንጋዮች ለማስቀመጥ የሚያገለገል ሲሆን፣ በብሉይ ኪዳን ዘመን የሚሠዉ የእንሥሳት ደም በታቦቱ ላይ ባለው የሥርዬት መክደኛ ላይ ይረጭ ነበር። በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ደመና ይታይ ስለነበር እግዚአብሔርም በሕጉ ላይ ሆኖ ይናገር ነበር።
ስለ ታቦት እና ስለ ጽላት ከላይ ያየነው መግለጫ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የተደረገ ነው። "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ዘንድ አኖረ” ዘጸ 40፥20 "ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደርግኋቸው እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ” ዘዳ 10፥5። እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ለሙሴ ሲሰጥ እንዲህ አስጠንቅቆት ነበር "እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም ከእርሱም አታጎድሉም” ዘዳ 4፥2-3።
ታቦት እንደዚህ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተሠራ ከሆነአሁን በኢትዮጵያ ያለውን ታቦት ምን ልንለው ነው? በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተሠራ ነውን?
ይህን መልስ ከመመላሳችን በፊት ስለ ኢትዮጵያ ታቦት አሠራር ከምስሉ ጋር እናሳያችሁ ከዚያ በመጽሐፍ ቅዱስ ከታዘዘው ታቦት ጋር አስተያዩና ፍርዳችሁን ስጡ።

የኢትዮጵያ ታቦት

1. ልኩና መጠኑ ብዛቱና ዓይነቱ ተለይቶ አይታወቅም፤

ከዋንዛ፣ ከወይራ፣ ወይም ሌላ ጠንከር ካለ እንጨት ሊሠራ ይችላል፣
በአሁኑ ሰዓት ከመቶ በላይ ታቦት ሊኖር ይችላል፤
ዙሪያውን ሐረግ ጥልፍ የመሰለ ሐረግ ይቀረጽበታል።
2. ስያሜው የማርያም፣ የሚካኤል፣ የገብርኤል ወዘተ ይባላል
በላዩ ላይ የሀገሩ ስም ተጽፎበታል ለምሳሌ የሰበታ ከሆነ ሰበታ ገብሬል ይላ
ዝቅ ብሎ የደብሩ አስተዳድሪ ወይም ቄሰ ገበዝ ስም ይጻፍበታል፣
ታቦቱ የተሰየመበት ሰው ስእል ይቀረጽበታል፣ ካላይ የሥላሴ ከታች የጻድቁ
3. በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ጽላት ወይም ታቦት ሊባል አይችልም፤
ጽላት እንዳይባል ከድንጋይ የተሠራ አይደለም፤ ከንጨትም ይሠራል፣
አሠርቱ ትእዛዝትም አልተጻፈበትም፣ ስእል ግን አለበት፣
ታቦት እንዳይባል እንደ ሳጥን የተሠራ አይደለም፤
እግዚአብሔር ካዘዘው ታቦት ጋር ብናስተያየው አንዱንም ቃል አያሟላም
4. አንዳድ ታቦቶች አልፋ ኦሜጋ የሚል ተጽፎባቸዋል፣
አንዳዶች ግን ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበርከክ የሚል ተጽፎበታል
አንዳዶች ምንም አልተጻፈባችውም እንዲሁ የሰው ሙያ ይታይባቸዋል።
5. ስለኢትዮጵያው ታቦት አሠራር በሔትኛውም መጽሐፍ አልታዘዘም፤
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ፈጽሞ የማናገኘው ሲሆን አዋልድ በሚባሉ መጽሕፍት ላይም ስለ አሠራሩ የተደነገጉ ሕጎች አላገኘንም እንኳንስ በእግዚአብሔር ትዛዝ የሰውም ትእዛዝልናገኘን አላቻልንም፣ ስለዚህ ማንም እንደየሙያው የሚሠራው ሆኖ አግኝተነዋል። የመጽሐፍ ቅዱሱ ታቦት በሙሴ አንድ ጊዜ ብቻ የተሠራ ሲሆን የኢትዮጵያው ታቦት ግን ሙያ ያለው ሁሉ በፈለገ ጊዜ ሊሠራው የሚችል ነው ለምሳሌ እኔ ከ10 በላይ ታቦት እየሠሩ የሚሸጡ ሰዎችን አውቃለሁ የሁሉም ሥራ እንደየችሎታቸው የተለያየ ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ ታቦት፤ ታቦትም ካልሆነ ጽላትም ካልሆነ ምን እንበለው ይሆን? አንዳዶች ለጊዜው ማምለጫ ይሆናል ያሉትን ትምህርት አዘጋጅተዋልለምሳሌ፣ የቅዱሳን መታሰቢያ ነው የሚሉ አሉ። ሥጋውና ደሙን ለመፈተት የምንጠቀምበት ገበታ ነው የሚሉም አሉ ይህ አባባል ትንሽ የሚያስመልጥ ይመስላል። እኛ ግን በጥንት ዘመን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ይሰጥ የነበረ መታወቂያ ወይም የፈቃድ ወረቀት ሠርተፊኬት ነበረ እንላልን። ማስረጃችንም በጽላቱ ላይ የተጻፈው የቄሰ ገበዙ ስም፣ የቦታው ወይም የደብሩ ስም፣ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኑ የተሰየመበት ቅዱስ ስም ነው። ይህ የሚያመለክተው ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም የተሰጠ ፈቅድ መሆኑን እንጂ በእርግጥ እንደ እግዚአብሔር ቃል የተሥራ ሆኖ ሊሰገድለት የሚገባ ነገር አይደለም።