ተዋዳጆች ሆይ፡- ሐዋያው ጳውሎስ ሮሜ8፡-34ን ‹‹ስለኛ የሚማልደው›› ብሎ እንጅ ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ሲል አለመጻፉን የጥንቷም ትሁን የዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታውቃለች!!
እራሷም ትመሰከራለች!! በ2000 ዓ/ም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለራሷ ባሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካለምንም
ምክንያት፤ በድፍረት ብቻ ‹‹ስለእኛ የሚማልደው›› የሚለውን ሐዋርያዊ ቃል በመሻር ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ተብሎ
ተቀይሮአል፡፡ ታዲያ ማዕቀብ መጣሉ ለምን አስፈለገ?? ሐዋርያው የተጠቀመው ሐረግ ‹‹ስለእኛ የሚማልደው›› በማለት
እንደሆነ እንጅ ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› አለማለቱን፤ የግሪኩን መጽሐፍ ተመልክተን የጥንቷም ትሁን የዘመኗ
ኦረቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይሄን እንደምታውቅ በአራት ማስረጃዎች እንገልጣለን፡-
1ኛ== ሁሉም እንደሚያውቀው ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፉት በግሪክ ቋንቋ ነው፡፡ በመሆኑም ዋናው ቁምነገር ያለው ይሄን ቃል ሐዋርያው በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምን ሲል እንደጻፈልን በሚገባ ማየቱ ላይ ስለሆነ በ“strong’s Hebrew And Greek dictionary” ላይ በማመሳከር የተቀመጠውን ቃል እንመልከት፡-
Rom 8፡-34 ‹‹Who is he that condemneth? It is Christ that died, yea rather, that is risen again, who is even at the right hand of God, who also maketh “INTERCESSION” for us.›› KJV. በአማርኛችን <<የሚማልደው>> በሚለው ቃል የተጻፈው፤ በኢንግሊዘኛው ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ <<INTERCESSION>> የሚለውን አቻ ቃል የያዘ ነው፡፡
Rom 8፡-34 ‹‹Who<3588><3588><5101> is | he that condemneth<2632>? It is | Christ<5547> | that died<599>, | yea<1161> | rather<3123>, | that is risen<1453> | again<2532>, | who<3739> | is<2076> | even<2532> | at<1722> | the right hand<1188> | of God<3588><2316>, | who<3739> | also<2532> | maketh “INTERCESSION <1793>” | for<5228> | us<2257>. |›› በዚህም መሰረት <<INTERCESSION>> የሚለው ቃል ወደ “strong’s Hebrew And Greek dictionary” የማመሳከሪያ ኮዶች ስናየው በቁጥር “INTERCESSION <1793>” ላይ የተመለከተው ሲሆን፤ ይሄን በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ቃል ወደ ኢንግሊዘኛ ሲፈታው እንዲህ የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠን፡-
<<1793 entugchano, en-toong-khan'-o>>:- deal with, make intercession.>> በዚህ መሰረት በግሪኩ ሐዋርያው ‹‹deal with, make intercession.›› የሚል ፍቺ ያለው ቃል የተጠቀመ ሲሆን ትርጉሙን ወደ አማርኛችን ስናመጣው ‹‹ማስማማት/ማስታረቅ/፣ ማማለድ/ምልጃ/›› የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠን እንጅ ስለ ፍርድ የሚያወራ አንዳችም ቃል ይቅርና የሚያስጠረጥርም ነገር አልተጠቀመም፡፡ ደግሞም በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ‹‹የሚፈርደው›› የሚለውን ቃል ሐዋርያቱ ምን የሚል ቃል እንደተጠቀሙ ማየቱ ነገሩን በይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ በዚህም መሰረት ‹‹የሚፈርደው›› የሚለውን ቃል በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን 1ጴጥ1፡-17 ላይ ‹‹ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው ==የሚፈርደውን== አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።›› የሚል እናገኛለን፡፡ ከዚህ ተነስተን ‹‹የሚፈርደውን›› ለሚለው ቃል በ“strong’s Hebrew And Greek dictionary” ላይ ስናመሳክረው፤ በኢንግሊዘኛው //judgeth// ለተባለው ቃል የግሪኩን አቻ ቃል በኮድ ቁጥር “2919” ላይ የተመለከተው ሲሆን፤ ቃሉም፡- <<krino, kree'-no>> የሚል ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ ሮሜ8፡-34ን በግሪኩ //የሚፈርደው// ብሎ ጽፎ ቢሆን ኖሮ፤ መጠቀም የነበረበት ‹‹krino, kree'-no›› የሚለውን ቃል እንጅ፤ //የሚማልደው// የሚለውን ‹‹entugchano, en-toong-khan'-o›› ቃል መጠቀም አልነበረበትም፡፡ ተዋዳጆች ሆይ፡- ታዲያ የሐዋርያውን ቃል ሽሮ፣ ሐዋርያቱ ያላስተማሩንን፣ እኛም ከቶ በማናውቀው፣ ጌታ መንፈስ ቅዱስ የማይከብርበትን፣ //የሚፈርደው// በተባለ እንግዳ ቃል፣ ማዕቀብ መጣሉ ለምን ያስፈለገ ይመስላችሃል??
2ኛ== የጥንቷ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈውን ‹‹ስለእኛ የሚማልደው›› ብላ እንደምታምን ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ይሄን በዕብ7፡-25 ‹‹ሊያማልድ›› ብሎ ሐዋርያው እንደጻፈ እንጂ ‹‹ሊፈርድ›› ብሎ እንዳልጻፈ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በድረሳኑ ላይ ሲያብራራ በግልጽ አስቀምጦታል አልነበረም፡-
#‹‹እመሰኬ ካህን ውእቱ አሜሃ ይተንብል፤ ወዘይቤሂ ጳውሎስ ይተንብል በእንቲአነ ዝኒ እስመ ሊቀ ካህናት ይተንብል፡፡ ወጊዜ ፈቀደ ይተንብል ሎሙ፤ ወአኮ በዝንቱ ጊዜ ባህቲቱ፤ አላ በእንተ ዘትመጽእ ሕይወት ዘለዓለም››
#በአማርኛ ሲተረጎም፡- ‹‹መለመኑ መማለዱ ሊቀ ካህናት ቢሆን እኮ ነው፡፡ ጳውሎስ ስለኛ **ይለምናል፣ ይማልዳል** ያለው የሊቀ ካህንነት ሥራ መለመን መማለድ በመሆኑ ነው፡፡ በወደደበት ጊዜ **ይለምናል ይማልዳል የሚለምነው የሚማልደው** በአሁኑ ጊዜ ብቻ አይደለም፤ ስለምትመጣውም ስለዘላለማዊት ሕይወትም **ይለምናል ይማልዳል** እንጅ፡፡›› ድርሳነ ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ 13ኛው ድርሳን ይመልከቱ፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡- ታዲያ ትውልድን ሁሉ የሚገድለው የዚህ አደገኛ ኑፋቄ ምንጩ ከወዴት ነው ትላላችሁ??
3ኛ== በ2000ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ያሳተመችው፤ የግዕዙን መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ተደርጎ ነው የተተረጎመ በማለት ሲሆን፤ የግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሚደግፋት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የግዕዙ መጽሐፍ ይሄን ሐረግ የተጠቀመው፡- “ይትዋቀሥ በእንቲኣነ” በሚል ሲሆን፤ ወደ አማርኛ በቀጥታ ሲተረጎም፡- “ስለ እኛ ይሟገታል ወይም ይከራከራል” የሚል ፍቺ ነው የሚሰጠው እንጅ ስለፍርድ የሚያወራ አይደለም፡፡ ለዚህ ማስረጃ የምናደርገው ቤተክርስቲያኒቱ የምትጠቀምበት ‹‹መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት›› የሚሰጠውን ፍች በማሳየት ይሆናል፡፡ “ተዋቀሠ” የሚለውን የግዕዙን ግስ ሲተረጎም፡- //በቁሙ (ተዋቀሠ)፣ ተሟገተ፣ ተከራከረ// የሚል ፍች ነው ያስቀመጠው እንጅ፤ ጭራሽ “የሚፈርደው” በማለት አልተረጎመውም (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ 401 ላይ ይመልከቱ)፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡- ታዲያ እያወቁ እንዳላወቁ በማስመሰል እንዲህ አይነት ክህደት በሕዝቡ ላይ መጫን ለምን ያስፈለገ ይመስላቹሃል??
4ኛ== ሌላውና በጣም የሚያሳዝነው ይህችው የዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለራሷ አስተምህሮ ስትል እየተንገዳገደ መድረሻውን ላጣው የስህተት ትምህርቷ ይደግፈኛል ብላ ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ስትል ብትተረጉመውም፤ በዚሁ በ2000ዓ/ም በታተመው መጽሐፍ ላይ ይሄን ሮሜ8፡-34 ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ያሉትን ቃል ለማብራራት፤ በግርጌ መግለጫ ላይ ያስቀመጠችው ‹‹//ግሪኩ ‹‹የሚማልደው›› ይላል//›› በማለት ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ፡- ታዲያ ይሄን መንፈሳዊ እውርነት ምን ትሉታላችሁ?? ዓይናቸው እያየች፣ ጆሮቸውም እየሰማች፣ የሐዋርያውን ቃል በመሻር ‹‹ስለእኛ የሚፈርደው›› ብሎ መጻፍ ምን የሚሉት ቅዠት ነው?? የሰው ልጅ የልቡ መደንደን በኃይል ሲበረታ፣ እራሱ ለፈጠራት አስተምህሮ፣ የአምላኩን ቃል ይሽራል፡፡ ለዚህ መልዕክት በማስረጃነት በተለቀቀው ፎቶ ላይ መመልከትና ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ታዲያ የህችን ቤተክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልግሻል ስትባል ልቧን አደንድና አያስፈልገኝ ስትል መስማት ምን ያህል ያሳፍራል!! ተሃድሶ ማለት ወደ ቀደመ መልክና ውበት ወደ ትክክለኛ ማንነት መመለስ፤ ከእንዲህ አይነቱ ከሳቱበትና ከጠፉበት የስህተተት ጎዳና በንስሃ ወደ አምላክ ሃሳብና ፈቃድ በመመለስ ሁሉን ቻዩ ለሆነው ጌታ ሁለተናን ማስገዛት ነው፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን፡- እግዚአብሔር ስለ ልጁ ኢየሱስ ሲል ምህረቱን ያብዛልን!! በምስኪኑ ሕዝብ ላይ የታወጀው ግፍ በጣም የሚያሳዝን፣ ልብም የሚያደማ፣ ማቅ የሚያስለብስ በንስሃ የሚያስጮኽ አረመኒየያዊ ድርጊት ነው፡፡
#ተወዳጆች ሆይ:- ሕሊናችሁ ለእውነት የሚወግንላችሁ ብቻ ልጠይቃችሁ እስቲ፣ ይሄ ማዕቀብ ምንድን ነው ትላላችሁ?? መርዘኛ የሆነውን የዲያብሎስን የጨለማ ሃሳቡንና ፈቃዱን፣ የምስኪኑን ሕዝብ ልብ አሳውሮ ወደ ሲኦል የሚነዳውን አደገኛ ግብሩን አታስተውሉምን?? የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስ ተገለጠ ተብሎ እንደተጻፈ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሄ ትውልድ ገዳይ ሥራው የፈረሰ የፈራረሰ ይሁን!! አሜን!! የተሃድሶ አገልግሎት ይሄን አደገኛ ኑፋቄ የታወጀበትንና የተበረዘውን ቃል ወደ ቀደመውና እውነተኛ ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል ተመልሶ ይተካ ዘንድ አንዱ ብርቱ ትግሉ ነው፡፡ ኢየሱስ እንጅ ማን ያሸንፋል?? አሜን በእግዚአብሔር ቃል ይተካል!

ተሃድሶ ለኦርቶዶክስ!
No comments:
Post a Comment